5 ተራሮች በሲና አምላክ በእግዚአብሔር ፊት፣በእስራኤልም አምላክ በእግዚአብሔር ፊት ተናወጡ።
6 “በዓናት ልጅ በሰሜጋር ዘመን፣በኢያዔል ጊዜ መንገዶች ባድማ ሆኑ፤ተጓዦችም በጠመዝማዛ መንገድ ሄዱ።
7 ለእስራኤል እናት ሆኜእኔ ዲቦራ እስክነሣ ድረስበእስራኤል ያለው የከተማ ኑሮ አበቃለት፤
8 አዳዲስ አማልክትን በተከተሉ ጊዜ፣ጦርነት እስከ ከተማው በር መጣ፤ጋሻም ሆነ ጦር፣በአርባ ሺህ እስራኤላውያን መካከል አልተገኘም።
9 ልቤ ከእስራኤል መሳፍንት፣ፈቃደኞችም ከሆኑ ሰዎች ጋር ነው፤እግዚአብሔር ይመስገን።
10 “እናንት በነጫጭ አህዮች የምትጋልቡ፣በባለ ግላስ ኮርቻ ላይ የምትቀመጡ፣በመንገድ ላይ የምትጓዙ፣በውሃ ምንጮች ዙሪያ ያለውን፣
11 የዝማሬ ድምፅ ስሙ።ይህም የእግዚአብሔር የጽድቅ ሥራ፣ጦረኞቹም በእስራኤል ያደረጉትን ያስታውሳል።“ከዚያም የእግዚአብሔር ሕዝቦች፣ወደ ከተማዪቱ በሮች ወረዱ፤