2 ባለጠጋና ድኻ የሚጋሩት ነገር፣ እግዚአብሔር የሁላቸውም ፈጣሪ መሆኑ ነው።
3 አስተዋይ ሰው አደጋ ሲያይ መጠጊያ ይሻል፤ብስለት የጐደለው ግን በዚያው ይቀጥላል፤ መከራም ያገኘዋል።
4 ትሕትናና እግዚአብሔርን መፍራት፣ሀብትን፣ ክብርንና ሕይወትን ያስገኛል።
5 በክፉዎች መንገድ ላይ እሾህና ወጥመድ አለ፤ነፍሱን የሚጠብቅ ግን ከእነዚህ ይርቃል።
6 ልጅን የሚሄድበትን መንገድ አስተምረው፤በሚሸመግልበት ጊዜ ከዚያ ፈቀቅ አይልም።
7 ባለጠጋ ድኻን ይገዛል፤ተበዳሪም የአበዳሪ ባሪያ ነው።
8 ክፋትን የሚዘራ መከራን ያጭዳል፤የቊጣውም በትር ይጠፋል።