5 “የእግዚአብሔር ቃል ሁሉ እንከን የለበትም፤እርሱ ለሚታመኑበት ሁሉ ጋሻቸው ነው።
6 በእርሱ ቃል ላይ አንዳች አትጨምር፤አለዚያ ይዘልፍሃል፤ ሐሰተኛም ያደርግሃል።
7 “እግዚአብሔር ሆይ፤ ሁለት ነገር እለምንሃለሁ፤እነዚህንም ከመሞቴ በፊት አትከልክለኝ፤
8 ሐሰትንና ሐሰት መናገርን ከእኔ አርቅልኝ፤ድኽነትንም ሆነ ብልጽግናን አትስጠኝ፤ብቻ የዕለት እንጀራዬን ስጠኝ።
9 ያለዚያ ግን ያለ ልክ እጠግብና እክድሃለሁ፤‘እግዚአብሔር ማን ነው?’ እላለሁ፤ወይም ድኻ እሆንና እሰርቃለሁ፤የአምላኬንም ስም አሰድባለሁ።
10 “አገልጋይን በጌታው ፊት በክፉ አታንሣው፤አለዚያ ይረግምህና ጒዳት ያገኝሃል።
11 “አባቱን የሚረግም፣እናቱን የማይባርክ ትውልድ አለ፤