ኢያሱ 6:20-26 NASV

20 መለከቱ ሲነፋ ሕዝቡ ጮኸ፤ የመለከቱ ድምፅ ተሰምቶ፣ ሕዝቡ በኀይል ሲጮኽ ቅጥሩ ፈረሰ፤ እያንዳንዱ ሰው ሰተት ብሎ ገባ፤ ከተማዪቱም በእጃቸው ወደቀች።

21 በከተማዪቱ ውስጥ ያለውን ሁሉ ማለትም ወንዱንና ሴቱን፣ ወጣቱንና ሽማግሌውን፣ ከብቱንና በጒን እንዲሁም አህያውን በሰይፍ ስለት ፈጽመው አጠፉ።

22 ኢያሱ ምድሪቱን የሰለሉትን ሁለቱን ሰዎች፣ “ወደ ጋለሞታዪቱ ቤት ሂዱ፤ በማላችሁላትም መሠረት እርስዋንና የእርሷ የሆነውን ሁሉ ከዚያ አውጡ” አላቸው።

23 ስለዚህ ሁለቱ ወጣት ሰላዮች ገብተው ረዓብን፣ አባቷንና እናቷን፣ ወንድሞቿንና የእርሷ የሆኑትን ሁሉ ከዚያ አወጧቸው። ቤተ ዘመዶቿንም ሁሉ አውጥተው ከእስራኤል ሰፈር ውጭ አስቀመጧቸው።

24 ከዚያም ከተማዪቱን በሙሉ፣ በውስጧ ያለውንም ሁሉ አቃጠሉ፤ ብሩንና ወርቁን፣ የናሱንና የብረቱን ዕቃ ግን በእግዚአብሔር ግምጃ ቤት አኖሩ።

25 ኢያሪኮን እንዲሰልሉ ኢያሱ የላካቸውን ሰዎች ስለ ደበቀች፣ ጋለሞታዪቱን ረዓብን፣ ቤተ ሰቧንና የእርሷ የሆኑትን ሁሉ አዳናቸው፤ እርሷም እስከ ዛሬ ድረስ በእስራኤላውያን መካከል ትኖራለች።

26 በዚያን ጊዜም ኢያሱ፣ እንዲህ ሲል ማለ፤ “ይህችን ከተማ መልሶ የሚሠራት ሰው በእግዚአብሔር ፊት የተረገመ ይሁን፤“መሠረቷን ሲጥል፣የበኵር ልጁ ይጥፋ፤ቅጥሮቿንም ሲያቆም፣የመጨረሻ ልጁ ይጥፋ” ብሎ ማለ።