12 ሕይወትን ሰጠኸኝ፤ በጎነትንም አሳየኸኝ፤እንክብካቤህም መንፈሴን ጠበቀ።
13 “ይህን ሁሉ ግን በልብህ ሸሸግህ፣ነገሩ በሐሳብህ እንደ ነበር ዐውቃለሁ፤
14 ኀጢአትን ብሠራ ትመለከተኛለህ፤መተላለፌንም ሳትቀጣ አታልፍም።
15 በደለኛ ብሆን ወዮልኝ፤ንጹሕ ብሆንም፣ ራሴን ቀና አላደርግም፤ውርደትን ተከናንቤአለሁና፤በመከራም ተዘፍቄአለሁ፤
16 ራሴን ከፍ ከፍ ባደርግ፣ እንደ አንበሳ ታደባብኛለህ፤አስፈሪ ኀይልህን ደጋግመህ ታሳየኛለህ፤
17 አዳዲስ ምስክሮችን ታመጣብኛለህ፤ቍጣህንም በላዬ ትጨምራለህ፤ሰራዊትህም ተከታትሎ ይመጣብኛል።
18 “ታዲያ ለምን ከማሕፀን አወጣኸኝ?ምነው ዐይን ሳያየኝ በሞትሁ ኖሮ!