15 በደለኛ ብሆን ወዮልኝ፤ንጹሕ ብሆንም፣ ራሴን ቀና አላደርግም፤ውርደትን ተከናንቤአለሁና፤በመከራም ተዘፍቄአለሁ፤
16 ራሴን ከፍ ከፍ ባደርግ፣ እንደ አንበሳ ታደባብኛለህ፤አስፈሪ ኀይልህን ደጋግመህ ታሳየኛለህ፤
17 አዳዲስ ምስክሮችን ታመጣብኛለህ፤ቍጣህንም በላዬ ትጨምራለህ፤ሰራዊትህም ተከታትሎ ይመጣብኛል።
18 “ታዲያ ለምን ከማሕፀን አወጣኸኝ?ምነው ዐይን ሳያየኝ በሞትሁ ኖሮ!
19 ምነው ባልተፈጠርሁ!ወይም ከማሕፀን ቀጥታ ወደ መቃብር በወረድሁ!
20 ጥቂት የሆነው ዘመኔ እያለቀ አይደለምን?ከሥቃዬ ፋታ እንዳገኝ ተወት አድርገኝ፤
21 ወደማልመለስበት ስፍራ፣ወደ ጨለማና ወደ ሞት ጥላ አገር ከመሄዴ በፊት፣