4 አንተ ዐይንህ የሥጋ ለባሽ ዐይን ነውን?ሟች የሆነ የሰው ልጅ እንደሚያይ ታያለህን?
5 ዘመንህ እንደ ሟች ሰው ዘመን ነውን?ወይስ ዓመታትህ እንደ ሰው ዓመታት ናቸውን?
6 ታዲያ፣ በደልን የምትፈላልግብኝ፣ኀጢአቴንም የምትከታተለው ለምንድን ነው?
7 እኔ በደለኛ እንዳልሆንሁ፣ከእጅህም ሊያስጥለኝ ማንም እንደማይችል አንተ ታውቃለህ።
8 “እጅህ አበጀችኝ፤ ሠራችኝም፤መልሰህ ደግሞ ታጠፋኛለህን?
9 እንደ ሸክላ እንዳበጀኸኝ አስብ፤አሁን ደግሞ ወደ ትቢያ ትመልሰኛለህን?
10 እንደ ወተት አላፈሰስኸኝምን?እንደ እርጎስ አላረጋኸኝምን?