7 እኔ በደለኛ እንዳልሆንሁ፣ከእጅህም ሊያስጥለኝ ማንም እንደማይችል አንተ ታውቃለህ።
8 “እጅህ አበጀችኝ፤ ሠራችኝም፤መልሰህ ደግሞ ታጠፋኛለህን?
9 እንደ ሸክላ እንዳበጀኸኝ አስብ፤አሁን ደግሞ ወደ ትቢያ ትመልሰኛለህን?
10 እንደ ወተት አላፈሰስኸኝምን?እንደ እርጎስ አላረጋኸኝምን?
11 ቈዳና ሥጋ አለበስኸኝ፤በዐጥንትና በጅማትም አገጣጥመህ ሠራኸኝ።
12 ሕይወትን ሰጠኸኝ፤ በጎነትንም አሳየኸኝ፤እንክብካቤህም መንፈሴን ጠበቀ።
13 “ይህን ሁሉ ግን በልብህ ሸሸግህ፣ነገሩ በሐሳብህ እንደ ነበር ዐውቃለሁ፤