10 “እርሱ ተከታትሎ መጥቶ በግዞት ቢያስቀምጥህ፣የፍርድ ሸንጎም ቢሰበስብ፣ ማን ሊከለክለው ይችላል?
11 በእውነት እርሱ ሸፍጠኞችን ያውቃል፣ክፋት ሲሠራም ልብ ይላል።
12 ጅል ሰው ጥበበኛ ከሚሆን ይልቅ፣የሜዳ አህያ ሰው ሆኖ ቢወለድ ይቀላል።
13 “ነገር ግን ልብህን ብትሰጠው፣እጅህንም ወደ እርሱ ብትዘረጋ፣
14 በእጅህ ያለውን ኀጢአት ብታርቅ፣ክፋትም በድንኳንህ እንዳይኖር ብታደርግ፣
15 በዚያን ጊዜ ሳታፍር ቀና ትላለህ፤ያለ ፍርሀት ጸንተህ ትቆማለህ፤
16 መከራህን ትረሳለህ፤ዐልፎ እንደሄደ ጐርፍም ታስበዋለህ።