2 “ይህ ሁሉ ቃል መልስ ማግኘት አይገባውምን?ወይስ ተናጋሪ ሰው እንደ እውነተኛ ይቈጠርን?
3 በውኑ የአንተ መዘላበድ ሰውን ዝም ያሰኛልን?ስታፌዝስ የሚገሥጽህ የለም?
4 እግዚአብሔርንም፣ ‘ትምህርቴ የጠራ፤በዐይንህም ፊት የጸዳሁ ነኝ’ ትለዋለህ።
5 ምነው እግዚአብሔር ቢናገርህ!ከንፈሩንም በአንተ ላይ ቢከፍት!
6 እውነተኛ ጥበብ ባለ ብዙ ፈርጅ ናትና፣የጥበብንም ምስጢር ምነው በገለጠልህ!እግዚአብሔር ለኀጢአትህ የሚገባውን እንዳላስከፈለህ ባወቅህ ነበር።
7 “የእግዚአብሔርን ጥልቅ ምስጢር ልትለካ ትችላለህን?ወይስ ሁሉን የሚችለውን አምላክ መርምረህ ትደርስበታለህን?
8 ከሰማይ ይልቅ ከፍ ይላል፤ ምን ልታደርግ ትችላለህ?ከሲኦልም ይጠልቃል፤ ምን ልታውቅ ትችላለህ?