5 ምነው እግዚአብሔር ቢናገርህ!ከንፈሩንም በአንተ ላይ ቢከፍት!
6 እውነተኛ ጥበብ ባለ ብዙ ፈርጅ ናትና፣የጥበብንም ምስጢር ምነው በገለጠልህ!እግዚአብሔር ለኀጢአትህ የሚገባውን እንዳላስከፈለህ ባወቅህ ነበር።
7 “የእግዚአብሔርን ጥልቅ ምስጢር ልትለካ ትችላለህን?ወይስ ሁሉን የሚችለውን አምላክ መርምረህ ትደርስበታለህን?
8 ከሰማይ ይልቅ ከፍ ይላል፤ ምን ልታደርግ ትችላለህ?ከሲኦልም ይጠልቃል፤ ምን ልታውቅ ትችላለህ?
9 መጠኑ ከምድር ይልቅ ይረዝማል፤ከባሕርም ይልቅ ይሰፋል።
10 “እርሱ ተከታትሎ መጥቶ በግዞት ቢያስቀምጥህ፣የፍርድ ሸንጎም ቢሰበስብ፣ ማን ሊከለክለው ይችላል?
11 በእውነት እርሱ ሸፍጠኞችን ያውቃል፣ክፋት ሲሠራም ልብ ይላል።