16 ብርታትና ድል ማድረግ በእርሱ ዘንድ ይገኛል፤አታላዩም ተታላዩም በእርሱ እጅ ናቸው።
17 አማካሪዎችን ከጥበባቸው ያራቍታል፤ፈራጆችንም ማስተዋል ይነሣል።
18 ነገሥታትን ድግ ያስፈታል፤ገመድም በወገባቸው ያስራል።
19 ካህናትን ከክህነታቸው ያዋርዳል፤ለዘመናት የተደላደሉትንም ይገለብጣል።
20 ዕውቅ መካሪዎችን ቋንቋ ያሳጣል፤የሽማግሌዎችንም ማስተዋል ይወስዳል።
21 የተከበሩትን ውርደት ያከናንባል፤ብርቱዎችንም ትጥቅ ያስፈታል።
22 የጨለማን ጥልቅ ነገሮች ይገልጣል፤የሞትንም ጥላ ወደ ብርሃን ያወጣል።