1 “ይህን ሁሉ ዐይኔ አይቶአል፤ጆሮዬም ሰምቶ አስተውያለሁ፤
2 እናንተ የምታውቁትን፣ እኔም ዐውቃለሁ፤ከእናንተ የማንስ አይደለሁም።
3 ነገር ግን ሁሉን ከሚችል አምላክ ጋር መነጋገር እፈልጋለሁ፤ከእግዚአብሔርም ጋር መዋቀስ እሻለሁ።
4 እናንተ ግን፣ በሐሰት የምትለብጡ ናቸሁ፤ሁላችሁ የማትረቡ ሐኪሞች ሆናችኋል።
5 ምነው ዝም ብትሉ!ያ ከጥበብ ይቈጠርላችሁ ነበር!
6 እንግዲህ ክርክሬን ስሙ፤የከንፈሬንም አቤቱታ አድምጡ።