16 ኀጢአተኛ በእርሱ ፊት መቅረብ ስለማይችል፤ይህ ድፍረቴ ለመዳኔ ይሆናል።
17 ቃሌን በጥንቃቄ አድምጡ፤እኔ የምለውንም ጆሮአችሁ በሚገባ ይስማ፤
18 እንግዲህ ጒዳዬን ይዤ ቀርቤአለሁ፤እንደሚፈርድልኝም ዐውቃለሁ።
19 ሊከሰኝ የሚችል አለ?ካለም፣ ዝም ብዬ ሞቴን እጠብቃለሁ።
20 “አምላክ ሆይ እነዚህን ሁለት ነገሮች ብቻ ስጠኝ፣ያን ጊዜ ከፊትህ አልሰወርም፤
21 እጅህን ከእኔ ላይ አንሣ፤በግርማህም አታስፈራራኝ፤
22 ከዚያ በኋላ ጥራኝ፤ እኔም እመልስልሃለሁ፤ወይም እኔ ልናገር፤ አንተ መልስልኝ።