21 እጅህን ከእኔ ላይ አንሣ፤በግርማህም አታስፈራራኝ፤
22 ከዚያ በኋላ ጥራኝ፤ እኔም እመልስልሃለሁ፤ወይም እኔ ልናገር፤ አንተ መልስልኝ።
23 በደሌና ኀጢአቴ ምን ያህል ነው?መተላለፌንና ኀጢአቴን አስታውቀኝ።
24 ፊትህን ለምን ትሰውራለህ?እንደ ጠላትህስ ለምን ትቈጥረኛለህ?
25 ነፋስ ያረገፈውን ቅጠል ታስጨንቃለህን?የደረቀውንስ እብቅ ታሳድዳለህን?
26 መራራ ነገር ትጽፍብኛለህ፤የወጣትነቴንም ኀጢአት ታወርሰኛለህ።
27 እግሬን በእግር ግንድ ታጣብቃለህ፤ውስጥ እግሬም ላይ ምልክት አድርገህ፣ዱካዬን አጥብቀህ ትከታተላለህ።