24 ፊትህን ለምን ትሰውራለህ?እንደ ጠላትህስ ለምን ትቈጥረኛለህ?
25 ነፋስ ያረገፈውን ቅጠል ታስጨንቃለህን?የደረቀውንስ እብቅ ታሳድዳለህን?
26 መራራ ነገር ትጽፍብኛለህ፤የወጣትነቴንም ኀጢአት ታወርሰኛለህ።
27 እግሬን በእግር ግንድ ታጣብቃለህ፤ውስጥ እግሬም ላይ ምልክት አድርገህ፣ዱካዬን አጥብቀህ ትከታተላለህ።