3 ነገር ግን ሁሉን ከሚችል አምላክ ጋር መነጋገር እፈልጋለሁ፤ከእግዚአብሔርም ጋር መዋቀስ እሻለሁ።
4 እናንተ ግን፣ በሐሰት የምትለብጡ ናቸሁ፤ሁላችሁ የማትረቡ ሐኪሞች ሆናችኋል።
5 ምነው ዝም ብትሉ!ያ ከጥበብ ይቈጠርላችሁ ነበር!
6 እንግዲህ ክርክሬን ስሙ፤የከንፈሬንም አቤቱታ አድምጡ።
7 ለእግዚአብሔር ብላችሁ በክፋት ትናገራላችሁን?ስለ እርሱስ በማታለል ታወራላችሁን?
8 ለእርሱ ታደላላችሁን?ለእግዚአብሔር ጥብቅና ልትቆሙ ነውን?
9 እርሱ ቢመረምራችሁ መልካም ነገር ይገኝባችኋልን?ሰውን እንደምታታልሉ፣ ልታታልሉት ትችላላችሁን?