13 “ምነው መቃብር ውስጥ በሰወርኸኝ!ቍጣህም እስከሚያልፍ በሸሸግኸኝ!ምነው ቀጠሮ ሰጥተህ፣ከዚያ በኋላ ባስታወስኸኝ!
14 ሰው ከሞተ በኋላ ተመልሶ በሕይወት ይኖራል?እድሳቴ እስከሚመጣ ድረስ፣ተጋድሎ የሞላበትን ዘመኔን ሁሉ እታገሣለሁ።
15 ትጠራኛለህ፤ እኔም እመልስልሃለሁ፤የእጅህንም ሥራ ትናፍቃለህ።
16 በዚያን ጊዜ በእርግጥ እርምጃዬን ትከታተላለህ፤ነገር ግን ኀጢአቴን አትቈጣጠርም።
17 መተላለፌ በከረጢት ይቋጠራል፤ኀጢአቴንም ትሸፍናለህ።
18 “ተራራ እንደሚሸረሸርና እንደሚወድቅ፣ዐለትም ከስፍራው እንደሚወገድ፣
19 ውሃ ድንጋይን እንደሚቦረቡር፣ጐርፍም ዐፈርን አጥቦ እንደሚወስድ፣አንተም የሰውን ተስፋ ታጠፋለህ።