17 መተላለፌ በከረጢት ይቋጠራል፤ኀጢአቴንም ትሸፍናለህ።
18 “ተራራ እንደሚሸረሸርና እንደሚወድቅ፣ዐለትም ከስፍራው እንደሚወገድ፣
19 ውሃ ድንጋይን እንደሚቦረቡር፣ጐርፍም ዐፈርን አጥቦ እንደሚወስድ፣አንተም የሰውን ተስፋ ታጠፋለህ።
20 አንድ ጊዜ ፈጽመህ ትበረታለህ፤ እርሱም ያልፋል፤ገጽታውን ትቀይራለህ፤ ትሸኘዋለህም።
21 ልጆቹ ቢከበሩ አያውቅም፤ቢዋረዱም አያይም።
22 የገዛ አካሉ ሕመም ብቻ ይሰማዋል፤ለራሱም ብቻ ያለቅሳል።”