5 የሰው ዕድሜ አስቀድሞ የተወሰነ ነው፣የወራቱንም ብዛት ወስነህ አስቀምጠሃል፤ሊያልፈው የማይችለውንም ገደብ አኖርህለት።
6 እንግዲህ ዘመኑን እንደ ምንደኛ እስኪፈጽም ድረስ፣ፊትህን ከእርሱ መልስ፤ ተወው።
7 “ዛፍ እንኳ ቢቈረጥ፣እንደ ገና ሊያቈጠቍጥ፣አዳዲስ ቅርንጫፍም ሊያበቅል ተስፋ አለው።
8 ሥሩ በምድር ውስጥ ቢያረጅጒቶው በመሬት ውስጥ ቢበሰብስም፣
9 የውሃ ሽታ ባገኘ ጊዜ ያቈጠቍጣል፤እንደ ተተከለም ችግኝ ቅርንጫፍ ያወጣል።
10 ሰው ግን ይሞታል፤ ክንዱንም ይንተራሳል፤ነፍሱም ትወጣለች፤ ከእንግዲህስ የት ይገኛል?
11 ውሃ ከባሕር ውስጥ እንደሚያልቅ፣የወንዝ ውሃም ጠፍቶ እንደሚደርቅ፣