10 በዕድሜ ከአባትህ የሚበልጡ፣የሸበቱ ሽማግሌዎች ከእኛ ጋር አሉ።
11 የእግዚአብሔር ማጽናናት፣በርጋታ የተነገረህ ቃል አነሰህን?
12 ልብህ ለምን ይሸፍታል?ዐይንህንስ ምን ያጒረጠርጠዋል?
13 በእግዚአብሔር ላይ እንድትቈጣ፣እንደዚህ ያለ ቃል ከአፍህ እንዲወጣ ያደረገህ ምንድን ነው?
14 “ንጹሕ ይሆን ዘንድ ሰው ምንድን ነው?ጻድቅስ ይሆን ዘንድ፣ ከሴት የተወለደ ምንድን ነው?
15 እነሆ፤ እግዚአብሔር በቅዱሳኑ እንኳ አይታመንም፤ሰማያትም በእርሱ ፊት ንጹሓን አይደሉም።
16 ታዲያ፣ ክፋትን እንደ ውሃ የሚጠጣ!አስጸያፊና ርኩስ ሰውማ እንዴት ይታመን!