24 ጭንቀትና ሐዘን ያስፈራሩታል፤ለማጥቃት እንደ ተዘጋጀ ንጉሥም ያይሉበታል፤
25 እጁን በእግዚአብሔር ላይ አንሥቶአልና፤ሁሉን የሚችለውን አምላክም ደፍሮአል፤
26 ወፍራምና ጠንካራ ጋሻ አንግቦ፣ሊቋቋመው ወጥቶአል።
27 “ፊቱ በስብ ቢሸፈን፣ሽንጡ በሥጋ ቢደነድንም፣
28 መኖሪያው በፈራረሱ ከተሞች፣የፍርስራሽ ክምር ለመሆን በተቃረቡ፣ሰው በማይኖርባቸው ወና ቤቶች ውስጥ ይሆናል።
29 ከእንግዲህ ባለጠጋ አይሆንም፤ ሀብቱም አይቈይም፤ይዞታውም በምድር ላይ አይሰፋም።
30 ከጨለማ አያመልጥም፤ቅርንጫፎቹን ነበልባል ያደርቃቸዋል፤በእግዚአብሔርም እስትንፋስ ይወሰዳል።