27 “ፊቱ በስብ ቢሸፈን፣ሽንጡ በሥጋ ቢደነድንም፣
28 መኖሪያው በፈራረሱ ከተሞች፣የፍርስራሽ ክምር ለመሆን በተቃረቡ፣ሰው በማይኖርባቸው ወና ቤቶች ውስጥ ይሆናል።
29 ከእንግዲህ ባለጠጋ አይሆንም፤ ሀብቱም አይቈይም፤ይዞታውም በምድር ላይ አይሰፋም።
30 ከጨለማ አያመልጥም፤ቅርንጫፎቹን ነበልባል ያደርቃቸዋል፤በእግዚአብሔርም እስትንፋስ ይወሰዳል።
31 በአጸፋው አንዳች አያገኝምና፤ከንቱን ነገር በመታመን ራሱን አያታልል።
32 ጊዜው ሳይደርስ ይጠወልጋል፤ቅርንጫፉም አይለመልምም።
33 ፍሬው በጮርቃነት እንደ ተለቀመበት የወይን ተክል፤አበባውም እንደ ረገፈበት የወይራ ዛፍ ይሆናል።