8 በእግዚአብሔር የመማክርት ጉባኤ ላይ ነበርህን?ጥበብስ የተሰጠው ለአንተ ብቻ ነው?
9 እኛ የማናውቀው አንተ ግን የምታውቀው ምን ነገር አለ?እኛስ የሌለን አንተ ያለህ ማስተዋል የቱ ነው?
10 በዕድሜ ከአባትህ የሚበልጡ፣የሸበቱ ሽማግሌዎች ከእኛ ጋር አሉ።
11 የእግዚአብሔር ማጽናናት፣በርጋታ የተነገረህ ቃል አነሰህን?
12 ልብህ ለምን ይሸፍታል?ዐይንህንስ ምን ያጒረጠርጠዋል?
13 በእግዚአብሔር ላይ እንድትቈጣ፣እንደዚህ ያለ ቃል ከአፍህ እንዲወጣ ያደረገህ ምንድን ነው?
14 “ንጹሕ ይሆን ዘንድ ሰው ምንድን ነው?ጻድቅስ ይሆን ዘንድ፣ ከሴት የተወለደ ምንድን ነው?