6 “ብናገር ሕመሜ አይሻለኝም፤ዝም ብልም አይተወኝም።
7 እግዚአብሔር ሆይ አሁንስ አድክመኸኛል፤ወገኖቼንም ሁሉ አጥፍተሃል።
8 ጭምትርትር ያደረግኸኝ ምስክር ሆኖብኛል፣ዐጥንቴን ያወጣው ክሳቴም ያጋልጠኛል።
9 በቍጣው ሰነጠቀኝ፤ በጥላቻው አስጨነቀኝ፣ጥርሱን ነከሰብኝ፤ባላጋራዬ ክፉ ዐይኑን ተከለብኝ።
10 ሰዎች በፌዝ አፋቸውን ከፈቱብኝ፤በንቀት ጒንጬን ጠፈጠፉኝ፤በአንድነትም በላዬ ተሰበሰቡ።
11 እግዚአብሔር ለክፉዎች አሳልፎ ሰጠኝ፤በጠማሞችም እጅ ጣለኝ።
12 በሰላም እኖር ነበር፤ እርሱ ግን ሰባበረኝ፤ዐንገቴን ይዞ አደቀቀኝ፤ማነጣጠሪያ ዒላማው አደረገኝ፤