1 መንፈሴ ደክሞአል፣ዘመኔ አጥሮአል፤መቃብርም ተዘጋጅቶልኛል።
2 አላጋጮች ከበውኛል፤ትኵረቴም ትንኰሳቸው ላይ ነው።
3 “እግዚአብሔር ሆይ፤ አንተ ተያዥ ሁነኝ፤ከአንተ ሌላ ዋስ የሚሆነኝ ማን አለ?
4 እንዳያስተውሉ ልባቸውን ይዘሃል፤ስለዚህ ድል አትሰጣቸውም።
5 ለጥቅም ሲል ወዳጁን የሚያወግዝ፣የልጆቹ ዐይን ይታወራል።
6 “እግዚአብሔር ለሰው ሁሉ መተረቻ፣ፊቱ ላይ የሚተፋበት ሰውም አደረገኝ።
7 ዐይኔ ከሐዘን የተነሣ ፈዘዘ፤መላ አካሌም እንደ ጥላ ሆነ።