3 “እግዚአብሔር ሆይ፤ አንተ ተያዥ ሁነኝ፤ከአንተ ሌላ ዋስ የሚሆነኝ ማን አለ?
4 እንዳያስተውሉ ልባቸውን ይዘሃል፤ስለዚህ ድል አትሰጣቸውም።
5 ለጥቅም ሲል ወዳጁን የሚያወግዝ፣የልጆቹ ዐይን ይታወራል።
6 “እግዚአብሔር ለሰው ሁሉ መተረቻ፣ፊቱ ላይ የሚተፋበት ሰውም አደረገኝ።
7 ዐይኔ ከሐዘን የተነሣ ፈዘዘ፤መላ አካሌም እንደ ጥላ ሆነ።
8 ቅኖች በዚህ ነገር ይደነግጣሉ፤ንጹሓንም በዐመፀኞች ላይ ይነሣሉ።
9 ጻድቃን ግን በያዙት መንገድ ይጸናሉ፤ንጹሕ እጅ ያላቸውም እየበረቱ ይሄዳሉ።