1 ኢዮብም እንዲህ ሲል መለሰ፤
2 “ነፍሴን የምታስጨንቋት፣በቃልስ የምትደቍሱኝ እስከ መቼ ነው?
3 እነሆ፤ ዐሥር ጊዜ ዘለፋችሁኝ፤ያለ ዕፍረትም በደላችሁኝ።
4 በእውነት ተሳስቼ ከሆነ፣ስሕተቱ የራሴ ጒዳይ ነው።
5 ነገር ግን ራሳችሁን በእኔ ላይ ከፍ ብታደርጉ፣መዋረዴንም እኔን ለመሞገት ብትጠቀሙበት፣
6 እግዚአብሔር እንደ በደለኝ፣በመረቡም እንደ ከበበኝ ዕወቁ።