7 “ ‘ተበደልሁ’ ብዬ ብጮኽ ማንም አይመልስልኝም፤ድምፄን ከፍ አድርጌ ባሰማም፣ ፍትሕ አላገኝም።
8 እንዳላልፍ መንገዴን ዘግቶአል፤መሄጃዬንም በጨለማ ጋርዶአል።
9 ክብሬን ገፍፎኛል፤ዘውዴንም ከራሴ ላይ ወስዶአል።
10 እስክወገድ ድረስ በሁሉ አቅጣጫ አፈራርሶኛል፤ተስፋዬንም እንደ ዛፍ ነቅሎታል።
11 ቍጣው በላዬ ነዶአል፤እንደ ጠላቱም ቈጥሮኛል።
12 ሰራዊቱ ገፍተው መጡ፤በዙሪያዬ ምሽግ ሠሩ፤ ድንኳኔንም ከበው ሰፈሩ።
13 “ወንድሞቼን ከእኔ አርቆአል፤ከሚያውቁኝም ተገለልሁ።