ኢዮብ 2:1-7 NASV

1 በሌላ ቀን ደግሞ፤ መላእክት በእግዚአብሔር ፊት ለመቆም መጡ። ሰይጣንም ከእነርሱ ጋር በእግዚአብሔር ፊት ሊቆም መጣ።

2 እግዚአብሔር ሰይጣንን፣ “ከወዴት መጣህ?” አለው።ሰይጣንም፣ “በምድር ሁሉ ዞርሁ፤ ወዲያና ወዲህም ተመላለስሁባት” ብሎ ለእግዚአብሔር መለሰ።

3 እግዚአብሔርም ሰይጣንን፣ “አገልጋዬን ኢዮብን ተመለከትኸውን? በምድር ላይ እንደ እርሱ ነቀፋ የሌለበት፣ ቅን፣ እግዚአብሔርን የሚፈራና ከክፋት የራቀ ሰው የለም፤ ያለ ምክንያት እንዳጠፋው ብትወተውተኝም፣ ይኸው ፍጹምነቱን እንደ ጠበቀ ነው” አለው።

4 ሰይጣንም እንዲህ ሲል መለሰ፤ “ ‘ቍርበት ስለ ቍርበት ነው’ እንዲሉ ሰው ለሕይወቱ ሲል ያለውን ሁሉ ይሰጣል፤

5 እስቲ እጅህን ዘርግተህ ዐጥንቱንና ሥጋውን ዳስ፤ በእርግጥ ፊት ለፊት ይሰድብሃል።”

6 እግዚአብሔርም ሰይጣንን፣ “እነሆ፤ እርሱ በእጅህ ነው፤ ሕይወቱን ግን እንዳትነካ” አለው።

7 ከዚህ በኋላ ሰይጣን ከእግዚአብሔር ፊት ወጥቶ ሄደ፤ ኢዮብንም ከእግር ጥፍሩ እስከ ራስ ጠጒሩ በክፉ ቍስል መታው።