4 ሰይጣንም እንዲህ ሲል መለሰ፤ “ ‘ቍርበት ስለ ቍርበት ነው’ እንዲሉ ሰው ለሕይወቱ ሲል ያለውን ሁሉ ይሰጣል፤
5 እስቲ እጅህን ዘርግተህ ዐጥንቱንና ሥጋውን ዳስ፤ በእርግጥ ፊት ለፊት ይሰድብሃል።”
6 እግዚአብሔርም ሰይጣንን፣ “እነሆ፤ እርሱ በእጅህ ነው፤ ሕይወቱን ግን እንዳትነካ” አለው።
7 ከዚህ በኋላ ሰይጣን ከእግዚአብሔር ፊት ወጥቶ ሄደ፤ ኢዮብንም ከእግር ጥፍሩ እስከ ራስ ጠጒሩ በክፉ ቍስል መታው።
8 ኢዮብም ገላውን ለማከክ ገል ወሰደ፤ በዐመድም ላይ ተቀመጠ።
9 ሚስቱም፣ “አሁንም ታማኝነትህን አልተውህምን? ይልቁን እግዚአብሔርን ርገምና ሙት!” አለችው።
10 እርሱም፣ “አነጋገርሽ እንደማታስተውል ሴት ነው፤ መልካሙን ነገር ከእግዚአብሔር ዘንድ ተቀበልን፣ ክፉውንስ አንቀበልምን? አላት።”በዚህ ሁሉ፣ ኢዮብ በንግግሩ አልበደለም።