10 ድንገተኛ አደጋ ያናወጠህ፤ወጥመድም ዙሪያህን የከበበህ ለዚህ ነው።
11 እንዳታይ ጨለማ የሆነብህ፣ጐርፍም ያጥለቀለቀህ ለዚህ ነው።
12 “እግዚአብሔር ከፍ ባለው ሰማይ የሚኖር አይደለምን?በሩቅ ከፍታ ያሉትን ከዋክብት ያያል!
13 ይህም ሆኖ ሳለ እንዲህ አልህ፤ ‘እግዚአብሔር ምን ያውቃል?በእንዲህ ያለ ጨለማ ውስጥስ ይፈርዳልን?
14 በሰማይ ክበብ ላይ ሲራመድ፣እንዳያየን ጥቅጥቅ ያለ ደመና ይሸፍነዋል።’
15 ኀጢአተኞች በሄዱባት፣በጥንቷ መንገድ እንደ ተመላለስህ ትቀራለህን?
16 ጊዜያቸው ሳይደርስ ተነጠቁ፤መሠረታቸውም በጐርፍ ተወሰደ።