16 ጊዜያቸው ሳይደርስ ተነጠቁ፤መሠረታቸውም በጐርፍ ተወሰደ።
17 እግዚአብሔርንም ‘አትድረስብን!ሁሉን የሚችል አምላክም ምን ያደርግልናል?’ አሉ።
18 ቤታቸውን በመልካም ነገር የሞላው ግን እርሱ ነው፤ስለዚህ ከኀጢአተኞች ምድር እርቃለሁ።
19 “ጻድቃንም የእነዚያን ጥፋት አይተው ይደሰታሉ፤ንጹሓንም እንዲህ ብለው ያፌዙባቸዋል፤
20 በእርግጥ ጠላቶቻችን ጠፍተዋል፤ሀብታቸውም በእሳት ተበልቶአል።’
21 “ለእግዚአብሔር ተገዛ፤ ከእርሱም ጋር ሰላም ይኑርህ፤በረከትም ታገኛለህ።
22 ምክርን ከአፉ ተቀበል፤ቃሉንም በልብህ አኑር።