4 “እርሱ የሚገሥጽህ፣ፍርድ ቤትም የሚያቀርብህ ስለምትፈራው ነውን?
5 ክፋትህ ታላቅ፣ኀጢአትህ ፍጻሜ የሌለው አይደለምን?
6 ያለ አንዳች ምክንያት ከወንድሞችህ መያዣ ወስደሃል፤ሰዎችን ገፈህ፣ ያለ ልብስ ዕራቍታቸውን አስቀርተሃል።
7 የዛሉትን ውሃ አላጠጣህም፤የተራቡትንም ምግብ ከልክለሃል።
8 ባለ ርስትና ኀያል፣በእርሱም የምትኖር ክቡር ሰው ብትሆንም፣
9 መበለቶችን ባዶ እጃቸውን ሰደሃል፤የድኻ ዐደጎችንም ክንድ ሰብረሃል።
10 ድንገተኛ አደጋ ያናወጠህ፤ወጥመድም ዙሪያህን የከበበህ ለዚህ ነው።