11 እግሮቼ እርምጃውን በጥብቅ ተከታትለዋል፤ፈቀቅ ሳልል መንገዱን ጠብቄአለሁ።
12 ከአፉ ከወጣው ትእዛዝ አልራቅሁም፣የአንደበቱን ቃል ከዕለት እንጀራዬ አብልጬ ይዣለሁ።
13 “እርሱ ግን ራሱን ችሎ ብቻውን የሚኖር ነው፤ የሚቋቋመውስ ማን ነው?እርሱ የፈቀደውን ያደርጋል።
14 በእኔ ላይ የወሰነውን ይፈጽማል፤ይህን የመሰለ ዕቅድም ገና ብዙ አለው።
15 በፊቱ የደነገጥሁትም ለዚህ ነው፤ይህን ሁሉ ሳስብ እፈራለሁ።
16 እግዚአብሔር ልቤን አባባው፤ሁሉንም የሚችል አምላክ አስደነገጠኝ።