3 እርሱን የት እንደማገኘው ባወቅሁ፤ወደ መኖሪያውም መሄድ በቻልሁ!
4 ጒዳዬን በፊቱ አቀርብ ነበር፤አፌንም በሙግት እሞላው ነበር።
5 የሚመልስልኝ ቃል ምን እንደሆነ ባወቅሁ ነበር፤የሚለኝንም ባስተዋልሁ ነበር።
6 በታላቅ ኀይሉ ከእኔ ጋር ይሟገት ይሆን?አይደለም፤ ይልቁን ያደምጠኛል።
7 ቅን ሰው ጒዳዩን በእርሱ ፊት ያቀርባል፤እኔም ከፈራጄ ለዘላለም ነጻ እሆናለሁ።
8 “ዳሩ ግን ወደ ምሥራቅ ብሄድ፣ በዚያ የለም፤ወደ ምዕራብም ብሄድ፣ እርሱን አላገኘውም፤
9 በሰሜን እየሠራ ሳለ አላየውም፤ወደ ደቡብ በሚዞርበት ጊዜ ደብዛው አይገኝም።