12 የሟቾች ጣር ጩኸት ከከተማዋ ይሰማል፤የቈሰሉት ሰዎች ነፍስ ለርዳታ ይጮኻል፤እግዚአብሔር ግን ተጠያቂዎቹን ዝም ብሎአል።
13 “በብርሃን ላይ የሚያምፁ፣ጐዳናውን የማያውቁ፣በመንገዱም የማይጸኑ አሉ።
14 ቀኑ ሲመሽ፣ ነፍሰ ገዳይ ይነሣል፤ድኾችንና ችግረኞችን ይገድላል፤በሌሊትም እንደ ሌባ ያደባል፤
15 አመንዝራ በዐይኑ ድንግዝግዝታን ይጠባበቃል፤‘ማንም አያየኝም’ ብሎ ያስባል፤ፊቱንም ይሸፍናል።
16 በጨለማ፣ ቤት ሰርስረው ይገባሉ፤በቀን ግን ይሸሸጋሉ፤ብርሃንንም አይፈልጉም።
17 ድቅድቅ ጨለማ ለሁላቸው እንደ ንጋት ነው፤አሸባሪውን ጨለማ ይወዳጃሉ።
18 “ይሁን እንጂ፣ በውሃ ላይ የሚኵረፈረፍ ዐረፋ ናቸው፤የወይን ቦታው ሰው የማይደርስበት፣ርስታቸው ርጉም ነው።