2 ሰዎች ድንበር ይገፋሉ፤የሰረቁትን መንጋ ያሰማራሉ።
3 የድኻ ዐደጉን አህያ ቀምተው ይሄዳሉ፤የመበለቲቱንም በሬ በመያዣነት ይወስዳሉ።
4 ችግረኛውን ከመንገድ ያስወግዳሉ፤የምድሪቱም ድኾች ይሸሸጋሉ።
5 በምድረ በዳ እንዳሉ የሜዳ አህዮች፣ድኾች ምግብ ፍለጋ ይራወጣሉ፤ከበረሓው ምድር ለልጆቻቸው ምግብ ይሻሉ።
6 ከሜዳ መኖ ይሰበስባሉ፤ከክፉዎች የወይን ቦታም ይቃርማሉ።
7 ዕራቍታቸውን ያለ ልብስ ያድራሉ፤በብርድም ጊዜ የሚለብሱት የላቸውም።
8 ከተራራ በሚወርድ ዝናብ በስብሰዋል፤መጠለያ አጥተው ቋጥኝ ዐቅፈዋል።