13 “እግዚአብሔር ለክፉው የመደበው ዕድል ፈንታ፣ግፈኛም ሁሉን ከሚችል አምላክ የሚቀበለው ቅርስ ይህ ነው፦
14 ልጆቹ የቱንም ያህል ቢበዙም ለሰይፍ ይዳረጋሉ፤ዘሩም ጠግቦ አያድርም።
15 የተረፉለትም በመቅሠፍት አልቀው ይቀበራሉ፤መበለቶቻቸውም አያለቅሱላቸውም።
16 ብርን እንደ ዐፈር ቢከምር፣ልብስንም እንደ ሸክላ ጭቃ ቢያከማች፣
17 እርሱ ያከማቸውን ጻድቃን ይለብሱታል፤ብሩንም ንጹሓን ይከፋፈሉታል።
18 የሚሠራው ቤት እንደ ሸረሪት ድር፣እህል ጠባቂም እንደ ቀለሰው መጠለያ ነው።
19 ሀብታም ሆኖ ይተኛል፤ ዘለቄታ ግን የለውም፤ዐይኑን በገለጠ ጊዜ ሀብቱ ሁሉ በቦታው የለም።