4 ከንፈሬ ኀጢአትን አትናገርም፤አንደበቴም ሽንገላ አይወጣውም።
5 እናንተን እንደ ቅኖች መቍጠር፣የማላደርገው ነገር ነው፤ ጨዋነቴንም እስክሞት ድረስ አልጥልም።
6 ጽድቄን አጥብቄ እይዛለሁ፤ አልለቀውምም፤በዘመኔም ሁሉ ኅሊናዬ አይወቅሰኝም።
7 “ጠላቴ እንደ በደለኛ፣ባላንጣዬም እንደ ክፉ ይሁን።
8 እግዚአብሔር ሲያስወግደው፣ነፍሱንም ሲወስድበት ዐመፀኛ ምን ተስፋ አለው?
9 በውኑ መከራ በገጠመው ጊዜ፣እግዚአብሔር ጩኸቱን ይሰማልን?
10 ሁሉን በሚችል አምላክ ደስ ይለዋልን?ዘወትርስ እግዚአብሔርን ይጠራልን?