11 የወንዞችን ምንጭ ይበረብራል፤የተሰወረውንም ነገር ወደ ብርሃን ያወጣል።
12 “ነገር ግን ጥበብ ከወዴት ትገኛለች?ማስተዋልስ መኖሪያዋ የት ነው?
13 ሰው ዋጋዋን አያውቅም፤በሕያዋንም ምድር አትገኝም።
14 ውቅያኖስ፣ ‘በእኔ ውስጥ የለችም’ ይላል፤ባሕርም፣ ‘በእኔ ዘንድ አይደለችም’ ይላል።
15 ንጹሕ ወርቅ ሊገዛት አይችልም፤ዋጋዋም በብር አይመዘንም።
16 በኦፊር ወርቅ፣በከበረም መረግድና በሰንፔር አትገመትም።
17 ወርቅም ብርሌም አይወዳደሯትም፤በወርቅ ጌጥም አትለወጥም።