25 ለነፋስ ኀይልን በሰጠ ጊዜ፣የውሆችን መጠን በለካ ጊዜ፣
26 ለዝናብ ሥርዐትን፣ለነጐድጓድም መንገድን ባበጀ ጊዜ፣
27 በዚያን ጊዜ ጥበብን ተመለከታት፤ ገመገማትም፤አጸናት፤ መረመራትም።
28 ከዚያም ሰውን፣‘እግዚአብሔርን መፍራት ጥበብ ነው፤ከክፋትም መራቅ ማስተዋል ነው’ አለው።”