3 ሰው፣ እስከ ጨለማ መጨረሻ ይዘልቃል፤ከድቅድቅ ጨለማ የማዕድን ድንጋይ ለማግኘት፣እስከ ውስጠኛው ዋሻ ገብቶ ይፈልጋል።
4 የሰው እግር ረግጦት በማያውቅበት ስፍራ፣ከሰዎች መኖሪያ ርቆ መውረጃ ጒድጓድ ይቈፍራል፤ሰው በሌለበት ቦታ ይንጠላጠላል፤ ይወዛወዛል።
5 ከላይዋ ምግብን የምታስገኝ ምድር፣ከታች በእሳት እንደሚሆን ትለዋወጣለች።
6 ሰንፔር ከዐለቷ ይወጣል፤ከዐፈሯም የወርቅ አንኳር ይገኛል።
7 ያን መንገድ ጭልፊት አያውቀውም፤የአሞራም ዐይን አላየውም፣
8 ኵሩ አራዊት አልረገጡትም፤አንበሳም በዚያ አላለፈም።
9 ሰው እጁን በቡላድ ድንጋይ ላይ ያነሣል፤ተራሮችንም ከሥር ይገለብጣል።