5 ከላይዋ ምግብን የምታስገኝ ምድር፣ከታች በእሳት እንደሚሆን ትለዋወጣለች።
6 ሰንፔር ከዐለቷ ይወጣል፤ከዐፈሯም የወርቅ አንኳር ይገኛል።
7 ያን መንገድ ጭልፊት አያውቀውም፤የአሞራም ዐይን አላየውም፣
8 ኵሩ አራዊት አልረገጡትም፤አንበሳም በዚያ አላለፈም።
9 ሰው እጁን በቡላድ ድንጋይ ላይ ያነሣል፤ተራሮችንም ከሥር ይገለብጣል።
10 በድንጋይ ውስጥ መተላለፊያ ያበጃል፤ዐይኖቹም የከበሩ ነገሮችን ሁሉ ያያሉ።
11 የወንዞችን ምንጭ ይበረብራል፤የተሰወረውንም ነገር ወደ ብርሃን ያወጣል።