12 ለርዳታ የሚጮኸውን ችግረኛ፣ድኻ ዐደጉንም ታድጌአለሁና።
13 በሞት አፋፍ ላይ የነበረ መርቆኛል፤የመበለቲቱንም ልብ አሳርፌአለሁ።
14 ጽድቅን እንደ ልብስ ለበስሁ፤ፍትሕም መጐናጸፊያዬና ጥምጥሜ ነበር።
15 ለዕዉራን ዐይን፣ለአንካሶችም እግር ነበርሁ።
16 ለችግረኛው አባት፣ለባይተዋሩ ተሟጋች ነበርሁ።
17 የኀጢአተኛውን ክራንቻ ሰበርሁ፤የነጠቀውንም ከጥርሶቹ አስጣልሁ።
18 “እኔም በልቤ እንዲህ አልሁ፤ ‘ዘመኔ እንደ አሸዋ በዝቶ፣በቤቴ ተደላድዬ እሞታለሁ፤