20 ክብሬ በውስጤ አዲስ እንደሆነ፣ቀስትም በእጄ እንደ በረታ ይኖራል።’
21 “ሰዎች ምክሬን በጸጥታ በመጠባበቅ፣በጒጒት አዳመጡኝ።
22 እኔ ከተናገርሁ በኋላ፣ የሚናገር ሰው አልነበረም፤ቃሌም እየተንጠባጠበ በጆሯቸው ይገባ ነበር።
23 ዝናብ እንደሚጠብቅ ሰው ጠበቁኝ፤ቃሌንም እንደ በልግ ዝናብ ጠጡ፤
24 በሣቅሁላቸው ጊዜ እውነት አልመሰላቸውም፤የፊቴም ብርሃን ብርቃቸው ነበር።