6 መንገዴ በቅቤ የራሰ ነበር፤ዐለቱም የወይራ ዘይት ያመነጭልኝ ነበር።
7 “ወደ ከተማዪቱ በር ብቅ ባልሁ ጊዜ፣በአደባባይዋም በወንበር በተቀመጥሁ ጊዜ፣
8 ጐበዛዝት አይተውኝ ገለል ይሉ፣ሽማግሌዎችም ተነሥተው ይቆሙ ነበር።
9 የሰፈሩ ታላላቅ ሰዎች ከመናገር ይቈጠቡ፣እጃቸውንም በአፋቸው ላይ ይጭኑ ነበር፤
10 የመኳንንት ድምፅ ጸጥ ይል፣ምላሳቸውም ከላንቃቸው ጋር ይጣበቅ ነበር፤
11 የሰሙኝ ሁሉ ያሞጋግሱኝ፣ያዩኝም ያመሰግኑኝ ነበር፤
12 ለርዳታ የሚጮኸውን ችግረኛ፣ድኻ ዐደጉንም ታድጌአለሁና።