1 ከዚህ በኋላ፣ ኢዮብ አፉን ከፍቶ የተወለደበትን ቀን ረገመ፤
2 እንዲህም አለ፤
3 “የተወለድሁበት ቀን ይጥፋ፣‘ወንድ ልጅ ተፀነሰ’ የተባለበት ሌሊት።
4 ያ ቀን ጨለማ ይሁን፤እግዚአብሔር ከላይ አይመልከተው፤ብርሃንም አይብራበት።
5 ጨለማና የሞት ጥላ ይውረሱት፤ደመናም በላዩ ላይ ይረፍ፤ብርሃኑን ጽልመት ይዋጠው።