16 ወይም እንደ ተቀበረ ጭንጋፍ፣ብርሃንም እንዳላየ ሕፃን በሆንሁ ነበር።
17 በዚያ ክፉዎች ማወካቸውን ይተዋሉ፤ደካሞችም በዚያ ያርፋሉ፤
18 ምርኮኞች እንደ ልባቸው ይቀመጣሉ፤ከእንግዲህም የአስጨናቂዎቻቸውን ጩኸት አይሰሙም።
19 ትንሹም ትልቁም በዚያ ይገኛል፤ባሪያው ከጌታው ነጻ ወጥቶአል።
20 “በመከራ ላሉት ብርሃን፣ነፍሳቸው ለተማረረች ሕይወት ለምን ተሰጠ?
21 ሞትን በጒጒት ለሚጠብቁና ለማያገኙት፣ከተሰወረ ሀብት ይልቅ ለሚሹት፣
22 ወደ መቃብር ሲቃረቡ ደስ እያላቸው፣በሐሤት ለሚሞሉ ሕይወት ለምን ተሰጠ?