2 እንዲህም አለ፤
3 “የተወለድሁበት ቀን ይጥፋ፣‘ወንድ ልጅ ተፀነሰ’ የተባለበት ሌሊት።
4 ያ ቀን ጨለማ ይሁን፤እግዚአብሔር ከላይ አይመልከተው፤ብርሃንም አይብራበት።
5 ጨለማና የሞት ጥላ ይውረሱት፤ደመናም በላዩ ላይ ይረፍ፤ብርሃኑን ጽልመት ይዋጠው።
6 ያ ሌሊት በድቅድቅ ጨለማ ይያዝ፤ከዓመቱ ቀናት ጋር አይቈጠር፤ከወራቱ በአንዱም ውስጥ አይግባ።
7 ያ ሌሊት መካን ይሁን፤እልልታም አይሰማበት።
8 ሌዋታንን ለማነሣሣት የተዘጋጁ፤ቀንንም የሚረግሙ ያን ቀን ይርገሙት።